አንድነታችንን እናጠናክር / Amharisch

የጸረ ዘረኝነት ህብረት – ለብዙሃን ማህበረሰብ!

ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ/ም

የጸረ ዘረኝነት የተግባር ቀን

በመላው ጀርመን የሚካሄድ የተቃውሞ መድረክ፡፡

በእያንዳንዱ ቀን የሚያጋጥሙ አዳዲስ የዘረኝነት አይነቶች አሉ፣ ግን ዘረኝነት ይጎዳል ዘረኝነት ህይወትን ያሳጣል፡፡ የአውሮፓን የውጭ ድንበሮች የመዝጋት ፖሊሲ ሆነ ሰዎች በሜድትሪያን ባህር ላይ እንዲሞቱ ማድረግ፣ አልያም ደግሞ በከተማ ማእከላት ሰዎችን በዘራቸው ብቻ ማግለል፣ ወይም አስገድዶ ስደተኞችን በካምፕ ውስጥ ማጎር፣ በሃይል ወደ ሃገራቸው መመለስ እና ያለ በቂ ምክንያት በቁጥጥር ስር ማዋል፣ አልያም ደግሞ መኖሪያ አካባቢያቸውን መበርበር እንዲሁም በሰው ሃብት ገበያው ላይ ፍትሐዊ ያልሆነ አያያዝ መተግበር፣ በትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚፈጸም መድሎ፣ የባለ ስልጣኖች የፍረጃ አሰራር፣ በመዝናኛ ስፍራ እና በኢንተርኔት ላይ የዘረኝነት ጥቃት ሁሉም ጎጂ እና ህይወትን የሚያሳጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ፖሊሲዎች ለዘረኝነት ግድያ እና ሽብር እርሾ እና መሰረት ናቸው፡፡ የዘረኝነት መዋቅር እንዲሁም አሰራር ማህበረሰብን ወደ ኋላ ጎታች በመሆኑ በሁላችንም የጋራ ትግል ልንቃወመው እና ልናስወግደው ይገባል፡፡

እንዲያም ሆኖ በሁሉም ስፍራዎች ሰዎች አዳዲሶችን የሚቀበል እና አንድነት ያለው ማህበረሰብ እንዲፈጠር በተቃራኒው ደግሞ ዘረኝነት እንዲወገድ በህብረት እየታገሉ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀን በትናንሽ ደረጃ እንዲሁም በትልቅ ደረጃ በተግባርና በፖለቲካ መስክ ትግል ይደረጋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ እንዲከበር፣ ለሁሉም እኩል መብት እንዲሰፍን እንታገላለን፡፡ ሰዎች በባህር ላይ ከመስጠም አደጋ እንዲድኑ እንታገላለን፡፡ እንዲሁም የጥቁሮች ህይዎት ዋጋ አለው (black lives matter) በሚል ስያሜ በፖሊስ የሚፈጸም ጥቃት እና የዘር መድሎ እንታገላለን፡፡ ለዜጎች የመኖሪያ ስፍራ የሚያገኙበት እና በህብረት የሚኖሩበት ከተማ እንዲኖር እንታገላለን፡፡ አስገድዶ ከሃገር የማስወጣት ፖሊሲን እንቃወማለን የሃይማኖት ተቋማት እና የዜጎች ጥገኝነት መብት እንዲከበር እንታገላለን፡፡ ማንኛውንም አይነት የዘር መድሎ እና ብዝበዛ እንቃወማለን፡፡ እንደ ስደተኞች የመብት ትግል እና የቀኝ ዘመም ጥቃት ተቃውሞ (MIGR antifa) ትግላችን በዘረኝነት ላይ የሚደረግ ትግል ነው፡፡ እኛ ብዙሃን እና ድምጻችንም ጎልቶ የሚሰማ፣ በከተሞች በገጠሮች፣ በጎዳናዎች፣ በግል መኖሪያ አካባቢያችን እንታገላለን መቼም አናቆምም!

የስደተኞች ትግል በማህበረሰባችን ውስጥ ለአስር አመታት አሻራውን ያሳረፈ እና የከተሞቻችን ታሪክና እውነታ አካል ሆኖ በዚህ ስፍራ እና በዚህ ጊዜ እና የብዙሃን ማህበረሰብ እየፈጠርን ስንሆን ማንም ሊያቆመን አይችልም!

የጸረ ዘረኝነት ህብረት – ለብዙሃን ማህበረሰብ! ሴፕቴምበር 5 ቀን ሁላችንም በጋራ ሆነን ወደ ጎዳናዎች በመውጣት በምን አይነት ማህበረሰብ ውስጥ ለመኖር እንደምንፈልግ ድምጻችንን በጉልህ እናሰማለን፡፤ እኛ የምንሻው ዘረኝነት የሌለበት ማህበረሰብ ነው! አሁን ከዚህ ቀደም “የተስፋ ሰልፍ” በሚል ርእስ ከዛሬ አምስት አመት በፊት ተገናኝተን ነበር ምክንያቱም ሴፕቴምበር 2015 የተስፋ ብርሃን የታየበት ነው፡፡ በወቅቱ የአገራት ድንበር ላይ የነበረው እገዳ ተነስቷል፡፡ አዳዲስ ማህበረሰቦች የተፈጠሩበት እና አዳዲስ ስደተኞች አውሮፓን የተቀላቀሉበት ለውጥ ታይቷል፡፡ የሚያደናቅፉን የዘረኝነት ህጎች እና ዛቻዎች ቢኖሩም አሁንም ቢሆን ትግላችን ይቀጥላል፡፡

እኛ የምናደርገው የጸረ ዘረኝነት ትግል ተጨባጭ ተግባር እና ግልጽ የሆነ ራእይ ያለው ነው፡፡ እኛ የምንታገለው በአውሮፓ ያሉ ከተሞች ሰዎች በህብረት እና በአንድነት የሚኖሩባቸው እንዲሆኑ ነው፡፡ እኛ የምንቃወመው ብዝበዛና ማግለልን ነው፡፡ እኛ የምንታገለው ባለንበት የመኖር፣ የመምጣት እና የመሄድ መብት ነው፡፡ እኩል መብት፣ ለሁሉም ሰው!

 

Afrique-Europe-Interact

AG Asylsuchende Sächsische Schweiz-Osterzgebirge e.V.

AK Asyl Friedrichsdorf

Aktionsbündnis gegen Abschiebungen Rhein-Main

Aktionsbündnis Solidarisches Salzwedel

Anti-Repression-Campaign you can’t evict solidarity

Arbeitskreis Asyl Cuxhaven e.V.

Aufstehen gegen Rassismus Rhein-Main

Bayerischer Flüchtlingsrat e.V.

Berlin Hilft

Bundes Roma Verband e.V.

Bündnis Alles Muss Man Selber Machen

Campana Cafe Mesoamerica CCM

Community for all, Darmstadt

eXchange e.V.

Flüchtlingsrat Baden-Württemberg e.V.

Flüchtlingsrat Hamburg e.V.

Flüchtlingsrat Niedersachsen e.V

Flüchtlingsrat Sachsen-Anhalt e.V.

Flüchtlingsrat Thüringen e.V.

Flüchtlingsrat Wiesbaden e.V.

Hamburger Bündnis gegen Rechts (HBgR)

Hessischer Flüchtlingsrat

Initiative “200 nach Marburg”

Initiative alle bleiben!

Karagah e.V.

kein mensch ist illegal, Hanau

Lübecker Flüchtlingsforum e.V.

Medibüro Berlin

Neag (noch eine autonome Gruppe) Bremen

Netzwerk SoliAsyl Thüringen

No Border Assembly

Open Arms

Rojava Solidarität Hanau

Roma Center e.V.

Sächsischer Flüchtlingsrat

Sea-Watch

Seebrücke

Seebrücke Frankfurt

Solidali-Frankfurt

Solidarische Provinz Wendland/Altmark

Solidarität Grenzenlos MTK

Solidarity City Kassel

Solizentrum Lübeck

VVN-BdA Hamburg

VVN-BdA Kreis Frankfurt

VVN/BdA Kreisvereinigung Oldenburg/Friesland

W.I.R Werdauer Initiative gegen Rassismus e.V.