አንድነታችንን እናጠናክር / Amharic

የጸረ ዘረኝነት ህብረት – ለብዙሃን ማህበረሰብ!

ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ/ም

የጸረ ዘረኝነት የተግባር ቀን

በመላው ጀርመን የሚካሄድ የተቃውሞ መድረክ፡፡

በእያንዳንዱ ቀን የሚያጋጥሙ አዳዲስ የዘረኝነት አይነቶች አሉ፣ ግን ዘረኝነት ይጎዳል ዘረኝነት ህይወትን ያሳጣል፡፡ የአውሮፓን የውጭ ድንበሮች የመዝጋት ፖሊሲ ሆነ ሰዎች በሜድትሪያን ባህር ላይ እንዲሞቱ ማድረግ፣ አልያም ደግሞ በከተማ ማእከላት ሰዎችን በዘራቸው ብቻ ማግለል፣ ወይም አስገድዶ ስደተኞችን በካምፕ ውስጥ ማጎር፣ በሃይል ወደ ሃገራቸው መመለስ እና ያለ በቂ ምክንያት በቁጥጥር ስር ማዋል፣ አልያም ደግሞ መኖሪያ አካባቢያቸውን መበርበር እንዲሁም በሰው ሃብት ገበያው ላይ ፍትሐዊ ያልሆነ አያያዝ መተግበር፣ በትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚፈጸም መድሎ፣ የባለ ስልጣኖች የፍረጃ አሰራር፣ በመዝናኛ ስፍራ እና በኢንተርኔት ላይ የዘረኝነት ጥቃት ሁሉም ጎጂ እና ህይወትን የሚያሳጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ፖሊሲዎች ለዘረኝነት ግድያ እና ሽብር እርሾ እና መሰረት ናቸው፡፡ የዘረኝነት መዋቅር እንዲሁም አሰራር ማህበረሰብን ወደ ኋላ ጎታች በመሆኑ በሁላችንም የጋራ ትግል ልንቃወመው እና ልናስወግደው ይገባል፡፡

እንዲያም ሆኖ በሁሉም ስፍራዎች ሰዎች አዳዲሶችን የሚቀበል እና አንድነት ያለው ማህበረሰብ እንዲፈጠር በተቃራኒው ደግሞ ዘረኝነት እንዲወገድ በህብረት እየታገሉ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀን በትናንሽ ደረጃ እንዲሁም በትልቅ ደረጃ በተግባርና በፖለቲካ መስክ ትግል ይደረጋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ እንዲከበር፣ ለሁሉም እኩል መብት እንዲሰፍን እንታገላለን፡፡ ሰዎች በባህር ላይ ከመስጠም አደጋ እንዲድኑ እንታገላለን፡፡ እንዲሁም የጥቁሮች ህይዎት ዋጋ አለው (black lives matter) በሚል ስያሜ በፖሊስ የሚፈጸም ጥቃት እና የዘር መድሎ እንታገላለን፡፡ ለዜጎች የመኖሪያ ስፍራ የሚያገኙበት እና በህብረት የሚኖሩበት ከተማ እንዲኖር እንታገላለን፡፡ አስገድዶ ከሃገር የማስወጣት ፖሊሲን እንቃወማለን የሃይማኖት ተቋማት እና የዜጎች ጥገኝነት መብት እንዲከበር እንታገላለን፡፡ ማንኛውንም አይነት የዘር መድሎ እና ብዝበዛ እንቃወማለን፡፡ እንደ ስደተኞች የመብት ትግል እና የቀኝ ዘመም ጥቃት ተቃውሞ (MIGR antifa) ትግላችን በዘረኝነት ላይ የሚደረግ ትግል ነው፡፡ እኛ ብዙሃን እና ድምጻችንም ጎልቶ የሚሰማ፣ በከተሞች በገጠሮች፣ በጎዳናዎች፣ በግል መኖሪያ አካባቢያችን እንታገላለን መቼም አናቆምም!

የስደተኞች ትግል በማህበረሰባችን ውስጥ ለአስር አመታት አሻራውን ያሳረፈ እና የከተሞቻችን ታሪክና እውነታ አካል ሆኖ በዚህ ስፍራ እና በዚህ ጊዜ እና የብዙሃን ማህበረሰብ እየፈጠርን ስንሆን ማንም ሊያቆመን አይችልም!

የጸረ ዘረኝነት ህብረት – ለብዙሃን ማህበረሰብ! ሴፕቴምበር 5 ቀን ሁላችንም በጋራ ሆነን ወደ ጎዳናዎች በመውጣት በምን አይነት ማህበረሰብ ውስጥ ለመኖር እንደምንፈልግ ድምጻችንን በጉልህ እናሰማለን፡፤ እኛ የምንሻው ዘረኝነት የሌለበት ማህበረሰብ ነው! አሁን ከዚህ ቀደም “የተስፋ ሰልፍ” በሚል ርእስ ከዛሬ አምስት አመት በፊት ተገናኝተን ነበር ምክንያቱም ሴፕቴምበር 2015 የተስፋ ብርሃን የታየበት ነው፡፡ በወቅቱ የአገራት ድንበር ላይ የነበረው እገዳ ተነስቷል፡፡ አዳዲስ ማህበረሰቦች የተፈጠሩበት እና አዳዲስ ስደተኞች አውሮፓን የተቀላቀሉበት ለውጥ ታይቷል፡፡ የሚያደናቅፉን የዘረኝነት ህጎች እና ዛቻዎች ቢኖሩም አሁንም ቢሆን ትግላችን ይቀጥላል፡፡

እኛ የምናደርገው የጸረ ዘረኝነት ትግል ተጨባጭ ተግባር እና ግልጽ የሆነ ራእይ ያለው ነው፡፡ እኛ የምንታገለው በአውሮፓ ያሉ ከተሞች ሰዎች በህብረት እና በአንድነት የሚኖሩባቸው እንዲሆኑ ነው፡፡ እኛ የምንቃወመው ብዝበዛና ማግለልን ነው፡፡ እኛ የምንታገለው ባለንበት የመኖር፣ የመምጣት እና የመሄድ መብት ነው፡፡ እኩል መብት፣ ለሁሉም ሰው!

የ5 ዓመታት የተስፋ ጉዞ፡ በህብረታችን እንዘልቃለን!

ዘረኝነት ገዳይ ነው፡ እንታገለዋለን!

በህብረታችን እንዘልቃለን እንቅስቃሴ ከነሐሴ 27 – 30 ቀን 2012 ዓ/ም

በሚደረገው “የጸረ ዘረኝነት ቀናት” ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ ያደርግላችኋል

ጥቁር አሜሪካዊው ጆርድ ፍሎዊድ በሚኒያፖሊስ

በፖሊስ መኮንኖች በግፍ ከተገደለ በኋላ የጥቁር ህይወት ዋጋ አለው የሚለው እንቅስቃሴ ጎዳናዎችን ተቆጣጥሯል፡፡ የእንቅስቃሴው መሪዎች እንዳሳዩት ዘረኝነት አለምአቀፍ ስርዓት መሆኑን እና ለማህበራዊ ለውጥ ፀረ ዘረኝነት ትግል ቁልፍ መሆኑን ነው፡፡ በአስደናቂ ሁኔታ በመላው አለም በተደረገ የተቋውሞ እንቅስቃሴ በግልፅ የተስተዋለው በትግሎቻችን መካከል እጅግ በርካታ ትስስሮች መኖራቸውን ነው፡፡ እኛ አዲስ፣ ሰፊ ትብብር ያለው የፍትህ፣ የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መብት ቅንጅት ያስፈልገናል፡፡ እያንዳንዳችን አንድ ውስን እንቅስቃሴነት መዝለል እና በሀገራት መካከል አዲስ የሆነ የጋራ መሰረት ለመመስረት መትጋት ይኖርብናል፡፡

አሁን ባለንበት የኮሮና ዘመን እዚሁ ነን፡፡ አሁንም በአውሮፓ፣ በጀርመን እና በሃኑ እንገኛለን፡፡ ምነም ሽብር፣ የነጭ አክራሪነት አንቀሳቃሾች ወይም የስደተኛ ባለስልጣን ይህንን እውነታ ሊቀይሩት አይችሉም፡፡ አሁንም እዚህ ነን፣ የየዕለት ትግላችንንም እንቀጥላለን፡፡ በዚህ ባለንበት የኮቪድ ጊዜ ሳይቀር መብቶቻቸው የተገፈፉባቸው፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ማጎሪያዎች እና ካምፖች ውስጥ ለመኖር የተገደዱ ሳይቀሩ እዚሁ ናቸው፣ አሁንም እዚህ ነን፣ የየዕለት ትግላችንንም እንቀጥላለን፣

ለመገንዘብ በሚያዳግት እና ጭካኔ በተሞላበት የውጭ ድንበሮች ክልከላ ፖሊሲ፣ በባህር ላይ እንዲሁም በየብስ ላይ በሚደረገው የመብት ገፈፋ የተነሳ፣ በብራስልስም ጥገኝነትን እና ከለላ የሚፈልጉ ሰዎች በተኩስ እንዲገደሉ የሚደነግግ ህግ ቢወጣ አሁንም እዚህ ነን፣ የየዕለት ትግላችንንም እንቀጥላለን፣

ሰላማዊ ሰዎች ያለምክንያት በመታሰራቸው እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ከሀገር እንዲወጡ በመደረጉ አሁንም እዚህ ነን፣ የየዕለት ትግላችንንም እንቀጥላለን፣

በከፋፋይ እና በአግላይ ፖሊሲ የተነሳ በዘረኝነት ምክንያት የሚፈጠሩ ግድያዎች እንዲሁም የአግላይነት አካሄድ በፈጠረው ውጤት አሁንም እዚህ ነን፣ የየዕለት ትግላችንንም እንቀጥላለን፣

በአሁኑ በየካቲት 19 በዚህ አመት 9 ሰዎች፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በዘረኛ የሽብር ጥቃት ህይወታቸው አልፏል፡፡ ይህንን ተከትሎ የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ሰነድ ለ10 አመታት ከህዝብ ተሰውሮ ቆይቷል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የዘረኞች ኔትዎርክ በፖሊስ እና በፖሊሲው ውስጥ ያላቸው ግንኙነት “Verfassungsschutz” እንዲቀጥል ተፈቅዶለታል፡፡

በተቋም ደረጃ ተግባራዊ የሚደረግ ዘረኝነት በየዕለት ህይወታችን ተፅእኖ አለው፣ በጽ/ቤቶች፣ በመንግስት ቢሮክራሲዎች ውስጥ፣ በፖሊስ፣ ቤት ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ክፍያ የሚያስገኝ ስራ ስናፈላልግ ተጽእኖ ያሳድርብናል፣ የአግላይነት አሰራር ዘረኝነት እንዲቆጠቁጥ በውጤቱም ዝቅተኛ ገቢ የሚያስገኙ እና ኢ መደበኛ ኢኮኖሚ ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዲበዘበዙ ምክንያት ይሆናል፡፡ ዘረኝነት በተለያዩ ብዙ ደረጃዎች ጎጂ እና ገዳይ ነው፡፡

በየዕለቱ በምናደርገው ተቋውሞ እና እንቅስቃሴ አላማ ይሄንኑ ማስወገድ፡፡ ይህንን የምንቋቋመው እና የምንቃወመው የህብረት እና የአንድነት መዋቅሩ እንዲለሙ እና እንዲስፋፉ በማድረግ ነው፡፡ ይህንን ዘረኝነት ለመቃወም በተቋውሞ ሰልፎች፣ ትርዒቶች እና ዘመቻዎች እራሳችንን እናደራጃለን፡፡ ሁሉንም አይነት ዘረኝነት አይነቶች የሚቃወም የማህበራዊ እንቅስቃሴ እየተጠናከረ ይገኛል፡፡ በምናቀርባቸው መብት ጥያቄዎች በመጉላት ላይ ናቸው፣ ባለንበት የመቆየት መብት እንዲሁም የህጋዊ ነዋሪነት ወረቀቶች ለሁሉም፣ በነፃነት የመንቀሳቀስ እንዲሁም ክፍት የሆኑ ድንበሮች፣ እኩል መብቶች ለሁሉም፡፡

በቅርብ ወራት # ማንም ሰው ወደኋላ እንዳይቀር (leave no one behind) የተሰኘው እንቅስቃሴ ተጀምሮ በሁሉም ስፍራ ተስፋፍታል፡፡ ይህ ትግል ሰብዓዊነት የጎደላቸውን በግሪክ ደሴቶች ላይ ያሉትን የትራንዚት ካምፖች ከስደተኛ ማጎሪያነት ነጥሎ ባዶ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አይነት መሰል ማጎሪያ ካምፖች እንዲዘጉ እና ምሀበራዊ ማግለል እንያከትም የሚጠይቅ ነው፡፡

የእኛ ትግል ወደ አንድነት እንመጣለን የሚለው ለፍትህ እና ለመብቶች የሚደረጉ ትግሎች ጥምረት ሲሆን በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተዋንያኖችን (የአካባቢ ጥበቃ እቅስቃሴ፣ የሴቶች መብት፣ አንቲፋ እንቅስቃሴ (ፀረፋሺዝም እንቅስቃሴ)፣ እንዲሁም ፀረ ሚሊተሪ እንቅስቃሴ) በአንድነት ያሰባሰበ ነው፡፡ እኛ እንደምናምነው በጋራ የምንጋራው ትልቅ ትግል አለ፡፡ ስለሆነም ሁላችንም በአንድነት ተሰባስበን ድርጊቶቻችንን አንድ ላይ እናቅድ፡፡

አለምአቀፉ ወቅታዊ ወረርሽኝ የፈጠረው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ በአንድነት ሆነን በእነዚህ የማህበረሰብ አውዶች የምናደርጋቸውን የመኖር ያለመኖር እጣፈንታችን የሚወሰንባቸውን ትግሎች እናስቀጥል፡፡ በመስከረም ወር መጀመሪያ ቀናት የምናደርገው ያልተማከለ የፀረ ዘረኝነት እንቅስቃሴ ላይ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪ እናደርጋለን፡፡

ከ5 ዓመታት በፊት በመስከረም 2007 ዓ/ም (2015) በአውሮፓ የነበረው የአግላይ ፖሊሲ የሆነው የድንበር ጥበቃ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ተደርጎበታል፡፡ ያኔ የተስፋ ጉዞ በሚል የተደረገው እንቅስቃሴ ድንበሮችን አልፈን መሻገር ለመቻላችን ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የስደት ፀደይ በሚል መጠሪያ የተደረገው እንቅስቃሴ ክፍት የሆነች አውሮፓን ለማለም መቻሉን ያረጋግጣል፡፡

እነዚህን ስኬታማ ልምዶች ማስታወስ እና በእነሱ ለይ ቀጣዩን ለመገንባት በመነሻነት ለሀገርአቀፍ እና ለድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴ ጥሪያችንን የምናቀርበው በመስከረም ወር የመጀመሪያ ሳምንት የተስፋ ጉዞ 5ኛ አመት መታሰቢያ በሚደረገው እንቅስቃሴ ትካፈሉ ዘንድ ነው፡፡

በዚህ በጣምራ በምናደርገው የእንቅስቃሴ ቀናት ትግሎቻችን እና ኔቶርኮቻችን አንፀባራቂ ብዝሃነታቸውን እናሳይ ዘንድ ነው፡፡ በተለያዩ ድርጊቶች፣ በተለያዩ ምናባዊ ስፍራዎች እንዲሁም በጎዳናዎች ላይ፣ በመተላለፊያዎች፣ በስደተኞች የጉዞ መስመሮች ስለ እንቅስቃሴ ነፃነት እና ስለ እኩል መብቶች ለመቃወም እና ሃሳባችንን ለመግለፅ እንሻለን፡፡

# ማንም ሰው ወደኋላ እንዳይቀር (leave no one behind) – ወደኋላ መቅረት አይኖርም፡፡

# ማንም ሰው ወደኋላ እንዳይቀር (leave no one behind) – የሚለው ትግል በግሪክ ደሴቶች የሚገኙትን ሰብዓዊነት የጎደላቸውን የስደተኞች ማጎሪያ እና የትራንዚት ካምፖች እዲዘጉ ብቻ ሳይሆን ሁሉም መሰል ካምፖች እንዲዘጉ እና ማህበራዊ ማግለል እንዲያከትም የሚጠይቅ ትግል ነው፡፡ በካምፖች የሚገኘው አቅጣጭ እውነታ፣ ይህም በግሪክ ደሴቶች አልያም በጀርመን እና አውሮፓ ባሉ ስፍራዎች ያለው ሁኔታ የሚያሳየው አሁን እንኳን በኮቪድ ዘመን፣ የእነማን ህይወት ጥበቃ እየተደረገለት፣ እነማን ደግሞ እንዲሞቱ የሚተው መሆናቸው ነው፡፡ እኛ የምንጠይቀው ካምፖቹ እንዲዘጉ እና ምቹ የሆነ መኖሪያ እንዲሰጠን ነው፡፡ እኛ የምንጠይቀው አንድም ሰው ወደኋላ እንዳይቀር፣ አንድም ሰው በካምፕ ለመኖር እንዳይገደድ ነው!

# አንድም ድንበር አይኑር – ከባህር እስከ ከተሞች

ከዚህ ስያሜ የምንረዳው በሜዲትራኒያን የሚደረገው የህይወት አድን ስራ የሚመለከት ሆኖ ስደተኞች ወደከተሞች መግባት እንዲችሉ እና በፈለጉት ከተማ ለመኖር እንዲችሉ የሚጠይቅ ነው፡፡ በባህር የህይወት አድን ኦፕሬሽን የሚሰሩት ከከንቲባዎች እና ከከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከባህር ሃይል ሰራተኞች እንዲሁም በህብረት የሚኖርባቸው ከተሞች ኢኒሼቲቮች ጋር በቅንጅት በመስራት የአንድነት ኮሪደሮችን ይመሰርታሉ፡፡

# አንድም ህገወጥ የለም – ሰዎችን አስገድዶ ከሀገር ማስወጣት ይቁም!

ሰዎችን አስገድዶ ከሀገር የማስወጣት ፖሊሲ ላይ የሚደረግ ተቃውሞ እንዲሁም ለመቆየት እና የመኖሪያ ወረቀቶችን ለማግኘት የሚደረግ የመብት ትግል በአውሮፓ ውስጥ በየዕለቱ የምናደርገው እና እንደዜጎች፣ በመጠለያ ስፍራዎች የሚደረግ ትግል አልያም ደግሞ እንደህግ እና የፖለቲካ ድጋፍ ወይም በጅምላ ከሀገር የማስወጣት ትግል ላይ የሚደረግ ነው፡፡

እኛ የምንታገለው አማራጭ መዋቅሮችን በመገንባት፣ ስደተኞች በካምፖች እና በማህበረሰቦች/ ኮሚዩኒቲ በራሳቸው እንዲደራጁ እና አደረጃጀቱን በማጠናከር እንዲሁም የከለላ መዋቅሮች እንዲፈጠሩ እና ተገድዶ ከሀገር ከመውጣት ራሳችንን ለመጠበቅ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ከተለያዩ የመብት ተሟጋች/አክቲቪስት/ ቡድኖች ጋር እንሰራን፡፡

# የስደተኞች ፀረ ፋሺስት ትግል (migrantifa) – ፀረ ዘረኝነት እና ፀረ የዘረኝነት ግድያ ትግል – የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አሁኑ ይወገድ!

በቅርብ ወራት ውስጥ የፀረ ፋሺስት ቡድኖች በተለያዩ አካባቢዎች ተመስርተዋል፡፡ እነዚህ ቡድኖች የፀረ ፋሺስት መደብት ጥያቄዎችን ከተለያዩ የስደተኞች ማህበረሰቦች ጋር የመብት ትግሎች ጋር ያስተሳስራሉ፡፡ የጥቁር ህይወት ዋጋ አለው የሚለው እንቅስቃሴ ያስመዘገበው ስኬት የሚያረጋግጠው የዘረኝነት ጉዳይ በተለይም መዋቅራዊ ዘረኝነት በሰፊው ማህበረሰብ ዘንድ መወያያ አድርጎታል፡፡ የቼሜኒስት፣ ሄል እና ካኑ የስኬት ተሞክሮዎች በሚኒያ ፖሊስ ወይም በሞሪያ ከታየው እውነታ ጋር ተሳስሯል፡ ተቋማዊ ዘረኝነት የየዕለት ህይወታችንን ተፅእኖ ውስጥ ሚከት ነው፣ በጽ/ቤቶች እና በመንግስት ቢሮፐክራሲ፣ በፖሊስ አሰራር፣ ማረፊያ እና ገቢ የሚያስገኙ ስራ ስናፈላልግ ተፅእኖ የሚያሳርፍብን ነው፡፡ ማህበራዊ አግላይነት የዘረኝነት ብዝበዛ የሚያብብበር መሰረት ሲሆን በተለይም አነስተኛ ገቢ የሚያስገኙ ሴክተሮች እና ኢ መደበኛ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ለብዝበዛ ያጋልጣል፡፡

በመ/ቤቶች ባለስልጣን ተቋማት እና በፐፖሊስ ወዘተ ውስጥ ያለው የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ እንዲከስም እንጠይቃለን፡፡

በአካባቢ ደረጃ ባልተማከለ መልኩ ከመስከረም 2-4 የሚደረግ እንቅስቃሴ!

በመስከረም ወር መጀመሪያ በአንድነት እንድንሰባሰብ እና ተግባሮቻችንን በጋራ እንድናቅድ፣ በከተሞች፣ በገጠሮች እና በዲስትሪክቶች በአንድነት እንድንሰራ እንፈልጋለን፡፡ አለምአቀፉ ወረርሽኝ የፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ አሁንም ድረስ ህብረት ያለው ማህበረሰብ ይፈጠር ዘንድ የምናደርገውን ዘርፈ ብዙ ትግል መቀጠላችንን ልናሳይ እንፈልጋለን፡፡ በርካታ ሃሳቦች አሉን ለምሳሌ ሰላማዊተቋውሞ፣ የተለያዩ መድረኮች፣ በኢሚግሬሽን ባለስልጣናት የሚደረግ ስራ ማቆም ወይም በክልል ደረጃ የሚደረግ ከገጠር ገጠር፣ ከካምፕ ካምፕ የሚደረግ የእግር ጉዞ ይህም በነፃነት የመንቀሳቀስን እና ባለንበት በሰላም የመኖር መብታችን እንዲከበር የምናደርገው ነው፡፡ እነዚህ የተቋውሞ ሰልፎች እና ተግባራት፣ ትርዒቶች፣ የኦንላይን እንቅስቃሴዎች ወይም የጎዳና ላይ ቲያትር ሁሉንም አማራጮችን ተጠቅመን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብታችን እንዲከበር፣ ለእኩል መብቶች እና በፀረ ዘረኝነት ትግል በህብረት እንድንቆም ጥሪ እንናቀርባለን፡፡

መስከረም 5

ለማዘጋጀት ምንፈልገው ያልተማከለ እና በሪጅን ደረጃ እንድንሰባሰብ ሲሆን በውጤቱም በተለያዩ የፌደራል እስቴቶች ወይም በሪጅን ማህበራት ደረጃ ጎን ለጎን ወደ አንድነት እንመጣለን የሚለውን እውን ለማድረግ እንዲሁም ብዝሃነታችን እና ጥንካሬያችን ጎልቶ እዲታይ እንሻለን፡፡

ዘረኝነትን ለመቃወም በህብረት ቆመናል፡፡